Tuesday, December 15, 2009

2009 Report on International Religious Freedom

ይህ ሪፖርት በሚከተለው የፕሬዚደንት ኦባማ ቃል ይጀምራል፦

"የሀይማኖት ነጻነት ለህዝቦች አብሮ መኖር ዋና ጉዳይ ነው"

ይህን ጽሑፍ በምናቀርበት በዚህ የገና በዓል ዋዜማ ወቅት የሙስሊሙ ዓለም በክሪስቲያኖች ነዋሪዎቹ ላይ የሚካሄደው ጥቃት ቀጥሏል። ክርስቲያኖች ሆኑ አይሁዶች፡ አቴይስቶች ሆኑ ሙስሊሞች ይህን በተመለከተ ድምጻቸውን በማሰማት ወይም ሶሊዳሪቲ ለማሳየት አሻፈረን ብለዋል።

ወደ አሜሪካው ሪፖርት ስንመለስ፡ ኢትዮጵያን አስመልክቶ የሚከተሉትን ዋና ዋና ዓረፍተነገሮች ከሰነዱ እንወስዳለን፦

ሽብርተኛ ቡድኖች ጥላቻቸውን በዓለም ዙሪያ እያስፋፉ ባሉበት በአሁኑ ዘመን ሀይማኖታዊ ነጻነት ለዓለም አቀር ደህንነት እጅግ ወሳኝ ነው።

የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ለሀይማኖት ነጻነት እውቅና የሚሰጥ ሲሆን ሌሎች ህጎችና ፖሊሲዎችም ለአጠቃላይ ነጻ የሀይማኖት እንቅስቃሴ አስተዋጽዖ አድርገዋል፡ መንግስቶ በአጠቃላይ ሀይማኖታዊ ነፃነትን በተግባር አስከብሯል፡ ሆኖም ግን አንዳንዴ የአካባቢ ባለስልጣናት ይህን ነጻነት ይጥላሉ (ሙስሊም ባለስልጣናት)

አልፎ አልፎ የሚፈጠሩ በሙስሊሞችና በክርስቲያኖች መካከል የሚታዩ ውጥረቶች ወደ ግጭት ያመሩበት ሁኔታ ነበር።

44 በመቶ የሚሆነው ህዝብ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን (ኢኦቤ) ተከታይ ሲሆን ከዚህም አብዛኛው የሚኖረው በሰሚናዊ የአገሪቱ ክፍል በትግራይና በአማራ ክልሎች ነው

ሰላሳ አራት በመቶው ህዝብ የሱኒ እስልምና ተከታይ ሲሆን ከዚህም አብዛኛው የሱፊ ትምህርት ተከታይ ነው። እስልምና አብዛኛው የሚገኘው በምስራቁ ክፍል በተለይም በሶማሌና አፋር ክልሎችና በኦሮምያ ብዙ ቦታዎ ነው። በቅርብ እያደገ የመጣ የወግ አጥባቂ ሙስሊሞች ቁጥር ቢኖርም ከአጠቃላዩ ሙስሊም ህብረተሰብ አንጻር ይህ ነው የሚባል አይደለም።

በህዳር 25 2001 በፀደቀው አዲስ የፕሬስ ህግ መሰረት አንድ ሀይማኖታዊ ቡድን ከሌላ ጋር እንዲጋጭ የሚደረግ ቅስቀሳ ወንጀል እንደሆነ ተደንግጓል። ህጉ በተጨማሪም የሀይማኖት መሪዎችን ስም የማጥፋት ተግባር እንደ ወንጀል እንዲቆጠርና ክስ እንዲመሰረትበት ያዛል።

በሰሜናዊ የአገሪቱ ክልል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እንደ ቅዱስ ከተማ በምትታየው በአክሱም ከተማ የሚገኙ የአካባቢው ባለስልጣናት እስካሁን ድረስ የከተማው ሙስሊሞች በተደጋጋሚ የሚጠይቁትን የመስጊድ መስሪያ ቦታ እንደከለከሏቸው ይገኛሉ። ሙስሊሞች በአክሱም ከተማ የግል መኖሪያ ቤትና ሀይማኖታዊ ያልሆኑ ህንፃዎችን ለመገንባት መሬት ያገኛሉ። የትግራይና የአማራ ክልላዊ መንግስታት ባለስልጣናት ሙስሊሞች መስጊድ ለመስራት ያቀረቡትን ጥያቄ አልተቀበሉም። ይህንን ውሳኒያቸውን የፊደራል መንግስቱ አልሻረውም። ለኢኦቤ ሌላ ቅዱስ ከተማ በሆነችው ላሊበላም የአካባቢው ባለስልጣናት ለመቃብር የሚሆን ቦታ እንጅ ለመስጊድ መስሪያ መሬት አልሰጡም።

መንግስት በህገ መንግስቱ ላይ የሰፈረው ሀይማኖትና መንግስት የተለያዩ ናቸው የሚለውን አንቀፅ የሚተረጉመው በመንግስትም ሆነ በግል ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሀይማኖታዊ ትምህርት አይሰጥም በሚል ነው። በካቶሊክ፡ በኦርቶዶክስ፡ በወንጌላውያንና በሙስሊም ቡድኖች በንብረትነት የተያዙና የሚተዳደሩ ትምህርት ቤቶች ሀይማኖትን እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ማስተማር አልተፈቀደላቸውም። ቤተክርስቲያኖች የሰንበት ትምህርት እንዲያስተምሩ ሲፈቀድ ቁርዓንን በመስጊድ ውስጥ ማስተማር ይቻላል። የመንግስት ትምህርት ቤቶችም ሀይማኖታዊ ባህሪይ ያላቸውን ክበቦች ለማቋቋም ፈቃድ ይሰጣሉ።

በሰኔ 23 ቀን 2001 በደሴ ከተማ ቤተክርስቲያን አላግባብ ለመገንባት የተደረገው ሙከራ እንዲቋረጥ ከተደረገ በኋላ ይህንን በመቃወም ሰልፍ በወጡ ሰዎች ላይ ፖሊስ ተኩሶ ሁለት ሰዎች ገድሏል። የግንባታውን ቦታ ሙስሊሞችም ለኛ መሆን አለበት ብለው ነበር። ብዙ ሰዎች በተፈጠረው ግርግር የተጎዱ ሲሆን አንዲት ሴትም ከገደል ወድቃ ሞታለች።

በሚያዝያ 16 ቀን 2001 ሙስሊሞች ሂጃብ እንዲለብሱና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ መስገድ እንዲችሉ መንግስት ፈቃድ እንዲሰጥ ለመጠየቅ ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉበት ጊዜ ፖሊስ ሰልፉን በመበተን 70 ተማሪዎችን ለአጭር ጊዜ በእስር አቆይቶ ነበር።

በህዳር 22 ቀን 2001 በጋሞ ጎፋ ዞን በአርባ ምንጭ ከተማ አንድ ቤተክርስቲያን አጠገብ እርስ በርስ በተጣሉ የኦርቶዶክስ ቄሶች ምክንያት በተቀሰቀሰ ግጭት ፖሊስ የተሰበሰቡትን ለመበተን ተኩስ ከፍቶ ሶስት ሰዎች አቁስሏል።

በየካቲት 9-10 እና በሚያዝያ 15-16 2001 የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በየክልሉ የአካባቢ ባለስልጣናት፡ የፀጥታ ቢሮዎችና የፖሊስ ኮሚሽነሮች ተካፋይ የሆነበት የምክክር መድረክ በማዘጋጀት በሀይማኖቶች መካከል ሊኖር ስለሚገባው መግባባትና የሀይማኖት ግጭቶችን ስለማስቀረት አወያይቷል።

በሀምሌ ወር 2000 በመንግስት የሚደገፍ የመያዶች በሀይማኖቶች መካከል ሰላም የመመስረት ጥረት አካል የሆነና የሰላም ባህል እንዲዳብር፣ በሀይማኖቶች መካከል የሚደረጉ ትብብሮችን የሚደግፍ፣ መተማመንና መልካም ግንኙነትን የሚያበረታታና ወደፊት ሊፈጠሩ የሚችሉ ግጭቶችን የሚከላከል ብሄራዊ የሀይማኖቶች የሰላም ምክር ቤት የሚል ተቋም ተመስርቷል።

በአብዛኞቹ ክልሎች ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች በአጠቃላይ ሲታይ አንዱ የሌላውን ሀይማኖት የሚያከብር ሲሆን አንዳንድ አካባቢዎች የተለያዩ ሀይማኖቶች ያሏቸው ጋብቻ ሲፈፅሙም ሆነ አንዱ ወደ ሌላው ሀይማኖት ሲቀየር እንደ ችግር አይታይም ነበር። ይሁን እንጅ አንዳንድ ህዝብ በብዛት የሰማቸው ሀይማኖታዊ ግጭቶች የነበሩ ሲሆን እነኝህም የመንግስትን ጣልቃ ገብነት የጠየቁ ነበሩ። በተጨማሪም አንዳንድ የሀይማኖት መሪዎችና የቤተክርስቲያን አባላት አካላዊ ጥቃትና የቃላት ማስፈራራት ስለደረሰባቸው የአካባቢው ባለስልጣናት እንዲከላከሉላቸው እስከ መጠየቅ ደርሰዋል።

የኢእጉበምቤ አንዳንድ በሳዑዲ አረቢያ የሚረዱ ሙስሊም ቡድኖች በክርስቲያኖችና በሙስሊሞች መካከል ቅራኔ ለማስፋፋት እንደሚንቀሳቀሱ በመግለጽ ስጋታቸውን በተደጋጋሚ አሰምተዋል። በሱፊ እስልምና ትምህርት የሚመሩትና በቁጥር የሚበልጡት ሙስሊሞች በሳዑዲ አረቢያ መያዶች ከሚረዱት ሙስሊም ቡድኖች ጋር ውጥረት ውስጥ የገቡበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር።

በመጋቢት ወር 2001 አንዳንድ የሙስሊም ቡድኖች ከምክር ቤቱ ፈቃድ ሳይጠይቁ ስብሰባ እንዳያካሂዱ የኢእጉበምቤ አግዷቸው ነበር።

በጥር 17 ቀን 2001 በሀይማኖት ሰበብ በተነሳ ግጭት ጎንደር ከተማ ውስጥ አንድ ፖሊስ ሲገደል ስምንት ሲቪሎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። እንደቀረበው ሪፖርት ግጭቱ የተነሳው ሙስሊሞች በኦርቶዶክስ እምነት ከፍተኛ ቦታ ባለው የጥምቀት በዓል ጊዜ ሁለት ታቦቶች የሚያርፉበት ቦታ ላይ መስጊድ መስራት በመጀመራቸው ነበር። ፖሊስ በወቅቱ 40 ሰዎችን ያሰረ ሲሆን ይህ ሪፖርት በተጠናቀረበት ወቅት እንደታሰሩ ነበሩ።

ከታህሳስ 30 እስከ ጥር 2 ቀን 2001 በድሬዳዋ ከተማ ተከታታይነት በነበራቸውና በየስፍራው በተቀሰቀሱ ሀይማኖታዊ ግጭቶች ሳቢያ አንድ ሰው ሲሞት 20 ቆስለዋል። እንደ ሪፖርት አቅራቢው በአንድ የከተማው ክፍል እስራዔል በጋዛ ላይ ያካሄደችውን ጥቃት በመቃወም ሙስሊም ወጣቶች በገና በዓል ላይ ሀይማኖታዊ መዝሙር እየዘመሩ በነበሩ ክርስቲያን ወጣቶች ላይ ድንጋይ ወርውረዋል። ክርስቲያን ወጣቶቹም አፀፋ በመመለስ ድንጋይ የወረወሩ ሲሆን ይህም ፖሊስ በስፍራው እስከደረሰ ድረስ ቀጥሎ ነበር። እንደነዚህ ዓይነት ግጭቶች ከአንዱ የከተማው ክልል ወደ ሌላው ተሰራጭተው ነበር።

በጥቅምት 26 ቀን 2001 ባለስልጣናት ብዛት ያላቸውን ቃወሪ የተባለ የሙስሊም ቡድን አባላት የሆኑ ሰዎችን 1998/99 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ኢሉባቡር፡ ጅማና ምዕራብ ወለጋ ውስጥ ክርስቲያኖችን በተጠና መንገድ በስፋት ለማጥቃት ተንቀሳቅሰዋል በሚል አስረዋል። በዚህ ሪፖርት መዝጊያ ጊዜ የነኝህ የታሰሩ ሰዎች ሁኔታ ምን እንደደረሰ አልታወቀም።

በህዳር ወር 2001 በሰቃ ቡዮ የሚገኙ የአካባቢ የመንግስት ባለስልጣናት በጥቅምት ወር 2000 ሙስሊሞች በ25 የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ቤተሰቦች ላይ ያደረሱትን ጥቃት በቅርቅ ጨርሰዋል።


ሙሉው ሪፖርት

No comments: